የኤጀንሲዉ ገጽታ

የኤጀንሲዉ ሥራ አስኪያጅ መልዕክት


 አቶ ደሳለኝ ወዳጄ ዘመነ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ኤጀንሲ በብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከተቋቋሙት መንግስታዊ ልማት ድርጅት ውስጥ አንዱ ሲሆን ፡ ኤጀንሲው ቀድም ሲል በብሔራዊ ክልሉ ከተሞች ውስጥ የሚታየውን የቤት እጥረት ለመፍታትና የከተሞችን ገፅታ ለመቀየር እዲሁም በግንባታው ዘርፍ ለዜጐች የስራ ዕድል በመፍጠር በመንግስት ቀጥተኛ ድጋፍ የመኖርያ ቤቶች ግባታው እንዲከናወን የክልሉ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 129/1998 የተቋቋመ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም ፕሮጀክቱ የተቋቋመበት የአምስት ዓመት የቆይታ ጊዜ ከመጠናቀቁም በላይ ጽ/ቤቱ በጊዜያዊነት ተሰጥቶት ከነበረው የተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም አስፈፃሚነት ተልዕኮ በተጨማሪ በቋሚነት የአነስተናና መካከለኛ ቤቶች ግንባታ በተጨማሪም በኮንስትራክሽን ዘርፍ በመሰማራት ለክልሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክትበትን ምቹ ሆኔተሰ ለመፍጠር በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡ ኤጀንሲው በክልሉ ውስጥ ለሚያካሄደው ተጨማሪ ...